Trendy:
                                                                                                                                                                                       LANGUAGES         AFAAN OROMOO         AMHARIC
Home NEWS AMHARIC

AMHARIC

News - amharic

አፍሪካን ከበለጸጉ አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በምርታማነት ረገድ ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል

አፍሪካን ከበለጸጉ አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በምርታማነት ረገድ ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል አዲስ አበባ ሰኔ 12/2005 አፍሪካን ከበለጸጉ አገሮች ተርታ ለማሰለፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ሥር ነቀል የፖሊሲ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አሳሰቡ፡፡ የአህጉሪቱን ዳያሰፖራ የገንዘብ ሃብት ለልማት ምንጭነት ለመጠቀም የፖሊሲ ማነቆዎችን ማላላት ያስፈልጋል አሉ፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ሶፊያን አህመድ ዛሬ የአፍሪካ ወጪና ገቢ ንግድ ባንክ 20ኛ የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ ሲከበር እንዳስገነዘቡት አህጉሪቱን ካለችበት ደረጃ ለማውጣት ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን ትኩረት ሊቸረው ይገባል፡፡ በዚህም የአህጉሪቱን የምርታማነት አቅም ማሳደግ እንደሚገባና አገሮቹ በአብዛኛው ከሚገኙበት የግብርናው ዘርፍ ወደ ኢንዱስትሪው በመሸጋገር እድገታቸውን ማፋጠን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ለዜጎቻቸው ምቹ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከድህነት አረንቋ ፈጥኖ በመውጣት መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታም እንደሚያስልፋቸው ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ኢኮኖሚ አሁንም በተፈጥሮ ሀብት ላይ ጥገኛ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ በዚህም ሳቢያ በጥሬ ዕቃዎች ላይ ያመዘነው የአህጉሪቱ የወጪ ንግድ ለኢንዱስትሪ ዕድገቱ ደካማነት አመላካች እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ በአህጉሪቱ እርስ በርሱ የሚመጋገብና የተቆራኘ የኢንዱስትሪ ልማት ማምጣት ዋነኛ አማራጭ መሆኑን ገልጸው በዚህ ረገድ አህጉራዊው የወጪና ገቢ ንግድ/አፍሪኤግዚም /ባንክ የተቋቋመበትን ዋነኛ ዓላማም ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ በባዕድ አገሮች የሚኖሩ ዜጎች ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ብቻ 60 ቢሊዮን ዶላር ወደ የአገሮቻቸው መላካቸውን የዓለም ባንክ መረጃን የጠቀሱት አቶ ሶፊያን፣ ከዚህ ውስጥ 28 ቢሊዮን ዶላር የአፍሪካውያን ድርሻ እንደሆንም ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከዳያስፖራ ዜጎች የገንዘብ ተጠቃሚ አምስት ዋነኛ አገሮች አንዷ መሆኗን አመልክተው፣ በውጭ የሚኖሩ አፍሪካውያን ለማህበረ- ኢኮኖሚ ልማት ያላቸው አስተዋዕኦ ክፍተኛ በመሆኑ ትኩረት እንደሚቸራቸው ተናግረዋል፡፡ የአፍሪካ ዳያስፖራ በየዓመቱ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አህጉሪቱ ከውጭ ብድርና ዕርዳታ ጋር እንደሚመጣጠን ገልጸዋል። ይህንን በውጭ ባንኮች የተከማቸ የገንዘብ ፈንድ ወደ አህጉሪቱ ለመሳብ አገሮች የአስተማማኝ የፋይናንስ ፖሊሲና ፕሮግራም መቅረጽ እንዳለባቸውም ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡ የአፍሪ ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳት ሚስተር ዣን ሉዊስ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ባንኩ ለኢትዮጵያና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ባንኮችና የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍና ብድር እየሰጠ ነው ፡፡ በኢትዮጵያ 20ኛ የምስረታ በዓሉን ሲያከብር ንግድና ኢንቨስትመንትን ወደ አገሪቱ ለመሳብ ጭምር በማለም መሆኑንም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የኃይል ፍላጎት ፕሮጀክቶች ውስጥም ገንዘቡን ኢንቨስት ማድረጉንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዓል ላይ ኤግዚቢሽንና የባህል ትዕይንት ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
 
News - amharic

ኢትዮጵያ ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ላለፉት ሁለት ቀናት ስታደርግ የነበረው ድርድር ውጤታማ በሆነ መልኩ ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ላለፉት ሁለት ቀናት ስታደርግ የነበረው ድርድር ውጤታማ በሆነ መልኩ ተጠናቀቀ አዲስ አበባ ሰኔ 12/2005 ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ላለá...
News - amharic

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ዓመታዊ የትምህርት ፌስቲቫል ተካሄደ

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ዓመታዊ የትምህርት ፌስቲቫል ተካሄደ አዲስ አበባ ሰኔ 12/2005  በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የትምህርት ልማት ሠራዊት በመገንባት የትምህርት ተ...
News - amharic

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከ38 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ ሆስፒታልና ጤና ጣቢያ እየተገነባ ነዉ

አዲስ አበባ ሰኔ 12/2005  በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአቤ ዶንጎሮ በጃርቴ ጃርደጋ ወረዳ ከ38 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር...
News - amharic

ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የእጣንና ሙጫ ምርት አልተጠቀመችበትም ተባለ

ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የእጣንና ሙጫ ምርት አልተጠቀመችበትም ተባለአዲስ አበባ ሰኔ 12/2005  ኢትዮጵያ ከፍተኛ እምቅ የእጣንና ሙጫ ሀብት ቢኖራትም በግንዛቤ እጥረት የተነሳ በ...
  • «
  •  Start 
  •  Prev 
  •  1 
  •  2 
  •  3 
  •  4 
  •  5 
  •  6 
  •  7 
  •  8 
  •  9 
  •  10 
  •  Next 
  •  End 
  • »
Page 1 of 464
YAADACHIISA HORDOFTOOTA WEBSAAYTII OROMIYAATIIF
Maxxansaalee adda addaa fi qophiilee dokimantariiwwan kan feenu waan ta'eef akka hordoftan isin affeerra!!!

Amharic latest