
የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽን የአፍሪካን እድገት እውን ለማድረግ መሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ለእድገቱ ቁልፍ መሆናቸውን በማመን እየሰራ ነው፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ፒ አይ ኦ ኤ/PIOA/ የተሰኘ ፕሮግራም ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
በሶስት ደረጃዎች ተከፋፍሎ እ.ኤ.አ እስከ 2040 የሚዘልቀው ይህ ፕሮግራም በትራንስፖርት፣ ኢነርጂ፣ መረጃና ሌሎች የመሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡
ኮሚሽኑ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት 51 ፕሮጀክቶቹን ለማስፈጸም 68 ቢሊዮን ዶላር መድቦ እየሰራ ነው፡፡
አፍሪካ በዚሁ ዘርፍ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ የዓለም ሀገራት እየደገፉ መሆናቸውንና ይህንን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም እኛ አፍሪካውያን ሰርተን ማሳየት አለብን ብሏል የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽን፡፡
LANGUAGES
አዲስ አበባ፣ግንቦት 13 የኢራኑ ፕሬዚዳንት መሀሙድ አህመዲነጃድ በ50ኛው የአፍሪካ ህብረት የምስረታ ክ...
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2005 ከጅቡቲ ወደብ ተጓጉዞ የሚመጣውን ኮንቴነር ሃገር ውስጥ ካሉ ደረቅ ወ...
አዲስ አበባ፣ግንቦት 12 የናይል የትብበር ማእቀፍ ስምምነት ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል...
ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዳሴና ለአፍሪካ እድገት እንዲሁም ለአለም ያበረከቷቸው የዲፕሎማቲክ...